የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በዛሬው ዕለት በዙም ቴክኖሎጂ በመታገዝ ባደረጉት የቪዲዮ ስብሰባ፡ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፤ ነገር ግን ኮሚቴው በአነጋጋሪው የአህጉራዊ የክለቦች ውድድሮች ውክልና ዙሪያ ምንም ያለው ነገር የለም።

በዛሬው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ፡ ህጋዊ ኮንትራት ላላቸው ተጫዋቾች ክፍያ መፈጸም እያለባቸው እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ያላደረጉ ክለቦች እስከ ሀምሌ 05 ቀን 2012ዓ.ም ድርስ ሀላፊነታቸውን ካልተወጡ፡ ምንም አይነት የተጫዋች ዝውውር እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳይሳተፉ ተወስኗል።

የክልል ፌዴሬሽኖችን አቅም ለማጠናከር የሚያግዝ የ2.8 ሚሊዬን ብር፡ እንዲሁም በችግር ላይ ለሚገኘው የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ጌታሁን መንግስቱ የ50,000ብር የገንዘብ ድጋፍ መደረጉም ታውቋል።

ፌዴሬሽኑ በቀጣዩ አመት የሚጀመሩ የሊግ ውድድሮችን በምን መልኩ ማካሄድ እደሚገባ የሚያጠና እና የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ያደረገ ሲሆን፡ ለ2013ቱ ጠቅላላ ጉባኤም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከወዲሁ እዲጀመሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በመጨረሻም የፌዴሬሽኑ የቀድሞ ዋና ጸሀፊ እያሱ መርሐጽድቅ (ዶ/ር) ስራ መልቀቅን ተከትሎ፡ ተቋሙን በጊዚያዊ የጽሕፈት ቤት ኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ባሕሩ ጥላሁን የፌዴሬሽኑ ዋና የጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።

የቀድሞው ጋዜጠኛ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽንስ ዲፓርትመንት ኃላፊ እና የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። በተጨማሪም የተቋሙ የክለብ ላይሰንሲንግ ማኔጀር የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ፍራንኮ በክለብ ላይሴንሲንግ ዳይሬክቶሬት ደረጃ እንዲሰሩም ተወስኗል፡፡

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *