ዲኤስቲቪ የታላላቆቹ የአውሮፓ የሊግ ውድድሮችን በድጋሚ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ሊጀምር ነው

የዲኤስቲቪ ጋዜጣዊ መግለጫ

“ግንቦት 29/2012 ዓ.ም – በቅርቡ የምንጀምረው የሰኔ ወር ለዲኤስቲቪ እና ስፖርት አፍቃሪ ለሆኑ ደንበኞቹ አዲስና አስደሳች ዜና ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ተከትሎ በመላው አለም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላለፉት ወራት ተገድበው የቆዩ ቢሆንም፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ሁኔታዎች የተወሰነ መሻሻል እያሳዩ በመምጣታቸው እንቅስቃሴዎች በልዩ ጥንቃቄ ታጅበው ቀስበቀስ ወደ መደበኛነት እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡

ይህንን ተከትሎም ሱፐር ስፖርት አዲስ በምንጀምረው የሰኔ ወር ውድድራቸውን ካቆሙበት እንደሚቀጥሉ ያረጋገጡትን ታላላቆቹን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የስፓኒሽ ላሊጋ እና የጣሊያን ሴሪ ኤ ፉክክሮች እንደተለመደው በቀጥታ ወደ እናንተ ለማሰተላለፍ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ሶስቱም ሊጎች እንደገና መጀመራቸውን ባለፈው ሳምንት ያበሰሩ ሲሆን የስፔን ላሊጋ በሱፐር ስፖርት ስክሪኖች ላይ ሀሙስ ሰኔ አራት ቀን በሴቪል ደርቢ ሴቪያ ከ ሪያል ቤቲስ በሚያደርጉት ጨዋታ መታየት ይጀምራል ቀሪዎቹ ዘጠኝ የሳምንቱ ጨዋታዎች ደግሞ ቅዳሜና እሁድ ይከናወናሉ፡፡

በስፔን ላሊጋ በታላላቆቹ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ መካከል የሚደረገው ፍልሚያ አሁንም አጓጊ እንደሆነ ቀጥሏል፤ በእነዚህ ታላላቅ ክለቦች መካካል ያለው የነጥብ ልዩነትም ሁለት ብቻ መሆኑ ፍልሚያውን ይበልጥ ተናፋቂ ያደርገዋል፡፡

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግም ከረቡእ ሰኔ 10 ቀን ጀምሮ ታላላቆቹ ክለቦች ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል፣ እንዲሁም አስቶን ቪላ እና ሼፊልድ ዩናይትድ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ካቆመበት ይቀጥላል፡፡

ሊጉን በሰፊ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ ሻምፒዮን ለመሆን ቢበዛ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ ማሸነፍ በቂው ነው: ይህንን ለማሳካትም ሊጉ በድጋሚ ሲመለስ ከከተማ ተቀናቃኙ ኤቨርተን ጋር አንድ ብሎ ፉክክሩን ይጀምራል።

ከፍተኛ የሻምፒዮንነት ትንቅንቅን እያስመለከተን የነበረው የዘንድሮው የጣሊያን ሲሪኤ ውድድርም ከሰኔ 9/2012 ዓ.ም ጀምሮ በአጓጊነቱ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።”

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *