የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ማለት ምን ማለት ነው?

በስፖርታዊ ውድድሮች ወይም እንቅስቃሴዎች ወቅት ሁለንተናዊ ብቃትን የሚጨምር የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዘዴዎችን በመጠቀም ያልተገባ ውጤት ማስመዝገብ ወይም ለማስመዝገብ መሞከር እና በአለም አቀፍ የጸረ-ዶፒንግ ህግ የተደነገጉ የህግ ጥሰቶችን መፈጸም ማለት ነው፡፡

በሀገራችንም ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት በስፖርቱ ዙሪያ እንዳይከሰቱ ለማድረግ እ.ኤ.አ ከ2014 ጀምሮ በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርና በአለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ጥያቄ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ በክትትልና ድጋፍ ደረጃ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ድርጅት (ETH-NADO) በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ስር በመሆን ስራውን ማከናወን የጀመረ ሲሆን፤ ከ2016 ወዲህ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 400/2009 ተቋቁሞ ስራውን በይፋ ጀመሯል፡፡

የጸረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ማለት ምንም ማለት ነው?

የጸረ አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት  ማለት፡ በማንኛውም አይነት መንገድ ጥፋት የፈጸመ ስፖርተኛም ይሁን ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ የሚሆንበትና እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከማንኛውም ውድድር እገዳ ሚጣልበት የህግ ስርአት ነው፡፡ ስለዚህም ማንኛውም ስፖርተኛ አበረታች ቅመሞችን ላለመጠቀምና ተጋላጭ ላለመሆን እራሱን የመጠበቅ  እና ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት አለበት።

የህግ ጥሰት የሚባሉትስ ምን ምን ናቸው?

– አትሌቱ በሰጠው ናሙና ውስጥ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችን ወይም ሜታቦሊክ ወይም ምልክት መገኘት

– የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችን መጠቀምና ለመጠቀም መሞከር

– ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆን

-የአድራሻ ምዝገባ (whereabouts information) ግዴታን አለመወጣት።

-የአበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥርን ማደናቀፍ ወይም ለማደናቀፍ መሞከር

– የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችን ወይም ዘዴዎችን ይዞ መገኘት

– የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችን ወይም ዘዴዎችን ማዘዋወር ወይም ለማዘዋወር መሞከር

-መተባበር  በውድድር ጊዜ ወይም ከውድድር ጊዜ ውጭ ጸረ- አበረታችን እንዲፈጸም መደገፍ

– የተከለከሉ ግነኙነቶችን ፈጽሞ መገኘት


– መረጃቹ የተገኙት ከ ETH-NADO ነው።

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *