የሃዘን መግለጫ – ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮችን ማለትም በኦሎምፒክና፣ በዓለም ሻምፒዮና ሀገሩን በመወከል የሚታወቀው የ22 ዓመት ወጣት አትሌት የሆነው አባዲ ሀዲስ በህመም ምክንያት በመቀሌ ሃይደር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 26/2012 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አትሌት አባዲ ሃዲስ በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ ልዩ ስሙ እንዳመሆኒ ወረዳ ጥር 27 1990 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን የአትሌቲክሰ ህይወቱን በእንዳመሆኒ የአትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ጣቢያ የጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በማይጨው አትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብቶ መደበኛ ስልጠናውን ሲያጠናቅቅ ትራንስ ኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ክለብ በመቀላቀል ህይወቱ እስካለፈበት እለት ድረስ በውጤታማነት ክለቡን፣ ክልሉንና ሃገሩ ሲያስጠራ የነበረ አትሌት ነው።

አባዲ እስካሁን ድረስ ካስመዘጋባቸው ድሎች ውስጥ፡

በኦሎምፒክ ጨዋታዎች

• በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በተካሄደው የ2016 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በ10000ሜትር በ27፡36.34 በሆነ ሰዓት 15ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና

• በዶካ ኳታር በተካሄደው የ2019 የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ5000ሜትር ተሳትፏል

• በለንደን በተካሄደው የ2017 የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ10000ሜትር በ26፡59.19 በሆነ ሰዓት 7ኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡

በዓለም አገር አቋራጭ

• በኡጋንዳ ካምላ በ2017 በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአዋቂ ወንዶች 10ኪ.ሜ. ውድድር በ28፡43 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃ በመያዝ የነሃስ ሜዳልያ አግኝቷል፡፡

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች

• በሞሮኮ ራባት በ2019 በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ10000 ሜትር በ28፡27.38 7ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን

በኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና

• በ2016 በተካሄደ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ10000ሜትር በ28፡43.2 በሆነ ሰዓት 1ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀበት ከተወዳደረባችው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የአትሌት አባዲ ሀዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በነገው እለት የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የትግራይ ክልል አትሌቲክሰ ፌዴሬሽንና የክለቡ አመራሮችና ሌሎች ኃላፊዎች በተገኙበት በትውልድ ስፍራው የሚከናወን ሲሆን፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላትና መላ ሰራተኞች የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን እየገለፁ ለቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናት ይመኛሉ፡፡

ልዩ ስፖርት ድረ-ገፅ ፡ በአትሌት አባዲ ሀዲስ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች፤ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹና መላው የአትሌቲክስ ቤተሰብ ልባዊ መጽናናትን ትመኛለች።

ነብስ ይማር!

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *