ዱባይ – ጥር 14/2012ዓ.ም – በየዓመቱ ጥር ወር አጋማሽ የሚከናወነው እና በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፉክክር እና በተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች የተለያዩ ግዛቶች በሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን አማካኝነት በልዩ ሁኔታ የሚደምቀው የዱባይ ማራቶን፡ ዘንድሮም እንደተለመደው ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ለድል አጭቶ፡ ነገ ማለዳ ከ11:00 ጀምሮ ለ21ኛ ጊዜ ይከናወናል።

ከሁለት አመት በፊት ውድድሩን ያሸነፈችው እና አምና የኢትዮጵያን የማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል 2:17:41 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ የወጣችው አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ “ከአምናው በበለጠ ጠንካራ ዝግጅት አድርጌ ለተሻለ ውጤት ነው አስቤ የመጣሁት፡ ነገር ግን ከሌሎቹ የሀገሬ ልጆች ቀላል ፉክክር እንደማይጠብቀኝም አውቃለሁ” ስትል፡ ትላንት በባለ ሰባት ኮከቡ ጁሜሪያህ ሆቴል በተዘጋጀው የቅድመ ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስተያዬቷን ሰጥታለች።

ብዙም የመናገር ድፍረት እንደሌለው የሚያስታውቀው እና በ2:04:40 የውድድሩ ባለ ፈጣን ሰዓት ተሳታፊ የሆነው ሰለሞን ደቅሲሳ በበኩሉ፡ ውድድሩን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ራሱን ዝግጅት እንደሚጠቀምበት አስታውቋል። በዘንድሮው ውድድር በሁለቱም ጾታወች ከቀረቡ 30 ስመጥር አትሌቶች መካከል 26ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ኢትዮጵያውያን በዚህ ውድድር ካላቸው የታሪክ እና የተሳታፊ አትሌቶች የቁጥር የበላይነት አንጻር፡ ዘንድሮም ድሉ የምስራቅ አፍሪካዋ የሯጮች ሀገር እንደሚሆን ብዙዎች ሀሳባቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። ያለፈው ዓመት የጌታነህ ሞላ ድልን ጨምሮ እስካሁን በተካሄዱ ያለፉት 20 ዓመታት የዱባይ ማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ለ13 እንዲሁም በሴቶች ደግሞ ለ14 ጊዜያት ያክል ማሸነፋቸውም ይታወቃል።

አዘጋጆቹ ይህንን ውድድር በሁለቱም ጾታ ለሚያሸንፉ አትሌቶች የ$100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) ሽልማት ያቀረቡ ሲሆን የዓለም ክብረወሰንን ለሚያሻሽሉ አትሌቶች ደግሞ የተጫማሪ $200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) እንደሚበረከትላቸው አስታውቀዋል።

ዱባይ ማራቶን የዋና አትሌቶች ውድድር የተሳታፊዎች ዝርዝር – ጥር 15/2012 ዓ.ም

ወንዶች

1. ሰለሞን ደቅሲሳ 🇪🇹 02:04:40

2. ሰይፉ ቱራ 🇪🇹 02:04:44

3. አንዷለም በላይ ሺፈራው 🇪🇹 02:06:00

4. አይቸው ባንቴ ደሴ 🇪🇹 02:06:23

5. ብርሃኑ በቀለ ባረጋ 🇪🇹 02:06:41

6. ልመንህ ጌታቸው ይዘንጋው🇪🇹 02:06:49

7. ይታያል አጥናፉ ዘሪሁን🇪🇹 02:07:00

8. አወቀ አያሌው 🇪🇹 02:07:12

9. ባለው ይሁንልህ ደርሰህ🇪🇹 02:07:22

10. በሻህ ይርሴ እስከዚያ🇪🇹 02:08:37

11. ይሁንልኝ አዳነ 🇪🇹 02:09:11

12. አብዲ ፉፋ🇪🇹 02:09:44

13. ተስፋዬ ሌንጮ አንበሴ 🇪🇹 02:10:49

14. ሆዜ ሉዊዝ ሳንታና ማሪን 🇲🇽 02:10:54

15. ሁዋን ዩኤል ፓቼሆ 🇲🇽 02:10:58

16. ኤሪክ ኪፕሩኖ ኪፕታኑይ 🇰🇪

ሴቶች

1. ወርቅኘሽ ደገፋ ደበሌ 🇪🇹 2:17:41

2. ብዙነሽ ዳባ ደጀኔ 🇪🇹 2:19:59

3. አለሙ መገርቱ 🇪🇹 2:21:10

4. በዳቱ ሂርፓ 🇪🇹 2:21:32

5. ደራ ዲዳ 🇪🇹 2:21:45

6. ጉተኒ ሾኔ 🇪🇹 2:23:32

7. ድባቤ ኩማ ለማ 🇪🇹 2:23:34

8. ትዕግስት አባይቸው ጃቦሬ 🇪🇹 2:24:15

9. ሀይማኖት አለማየሁ 🇪🇹 2:25:51

10. የኔነሽ ጥላሁን ድንቄሳ 🇪🇹 2:25:54

11. ኦብሴ አብደታ 🇪🇹 2:27:47

12. ጫልቱ ጣፋ ዋቃ 🇪🇹 2:29:30

13. ሀና ሊንድሆልም 🇸🇪 2:29:34

14. ሀዊ ፈይሳ 🇪🇹

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *