አዲስ አበባ – ህዳር 05/2012ዓ.ም – በየዓመቱ ከፍተኛ ፉክክር የሚስተናገድበት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የታዋቂ አትሌቶች አለም አቀፍ የ10ኪሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዘንድሮም ከ500 በላይ አትሌቶችን በሁለቱም ጾታዎች በማሳተፍ የፊታችን እሁድ ህዳር 07 ይከናወናል።

ለ19ኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ: ኬንያውያን፣ ዩጋንዳውያን እና ኤርትራውያን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፡ ለውጤት ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል ስለተወሰኑት ጥቂት ልንላችሁ ወደናል።

በሴቶች ውድድር

ሀዊ ፈይሳ – መከላከያ

– የ2009 እና 2010 ዓ.ም የ5000ሜ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ፡፡

– በ5000ሜ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ – በ2011 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና

– 5000ሜ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ በሞሮኮው የአፍሪካ ጨዋታዎች፡፡

– በዶሃው የአለም ሻምፒዮና በርቀቱ 8ኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

ያለምዘርፍ የኋላ – ግሎባል ስፖርት

– በሞሮኮው የአፍሪካ ጨዋታዎች በግማሽ ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ፡፡

– በ2011 ሚያዚያ ወር ላይ ሞሮኮ ራባት በተካሄደ ሌላ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸንፋለች፡፡

– ከአንድ ወር በፊት በተካሄደው የዴልሂ ግማሽ ማራቶን ውድድር በጸሀይ ገመቹ በአንድ ሰከንድ ብቻ ተቀድማ 2ኛ ወጥታለች

– የ2011 ዓ.ም የታላቁ ሩጫ 5ኪሜ ቅደሚያ ለሴቶች ውድድርን በ4ኛነት አጠናቃለች፡፡

ሹሬ ደምሴ – ኦሮሚያ ፖሊስ

– የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10000ሜ አሸናፊ

– በ2011ዓ.ም መጋቢትት ወር ላይ የተካሄደውን የቶኪዮ ማራቶን ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡

– ጥቅምት 2011 ዓ.ም የተካሄደውን የቺካጎ ማራቶን በሶስተኛነት አጠናቃለች፡፡

– በ2009 ዓ.ም በዱባይ ማራቶን 2ኛ ሆና አጠናቃለቸ

አበሩ ዘውዴ – ጌታ ዘሩ

– በ2007ዓ.ም – በታላቁ ሩጫ ውድድር 19ኛ

– በ2006 ህዳር ላይ በህንድ የተካሄደውን የፑኔ ግማሽ ማራቶን በአንደኛነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

አበራሽ ምንስዎ – ሱር ኮንስትራክሽን

– በ3000ሜ የአለም ከ18 ዓመት በታች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ፡ 2009 ሰኔ ወር በኬኒያ በተካሄደ ውድድር።

– በተመሳሳይ ርቀት ሀምሌ 2010 አልጀሪያ ላይ በተካሄደ የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ፡፡

ፎቴን ተስፋይ – መሶቦ ሲሚንቶ

– የ 2009 ዓ.ም የአለም ከ20 አመት በታች የሀገር አቋራጭ ውድድርን በ4ኛነት አጠናቃለች፡፡

– የ2009 እና 2011 የታላቁ ሩጫ ውድድር አሸናፊ ስትሆን ዘንድሮ የምታሸንፍ ከሆነ ከውዴ አያሌው ጋር የውድድሩ ብዙ ጊዜ አሸናፊነት ክብርን የምትጋራ ይሆናል፡፡ ውዴ የ2001፣2002 እና 2007 ዓ.ም አሸናፊ ነች፡፡

– የአምናውን ድሏን የምትደግም ከሆነ፡ ገነት ጌታነህ 1997 እና 1998 እንዲሁም ውዴ አያሌው 2001 እና 2002 በተከታታይ ጊዜ በማሸነፍ የያዙትን ክብረወሰን የምትጋራ ይሆናል፡፡

አለሚቱ ታሪኩ – ኦሮሚያ ክልል

– በሞሮኮው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ5000ሜ ሶስተኛ

– በ48ኛው (2011ዓ.ም) የኢትዮጵያ ሻምፒዮና በ5000ሜ የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ

– በዴንማርኩ የአለም አገር አቋራጭ ውድድር (2011ዓ.ም) ከ20 ዓመት በታች የብር ሜዳሊያ አሸናፊ፡፡

በወንዶች ውድድር

አንዳምላክ በልሁ – ሲዳማ ቡና

– የ2009ዓ.ም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10000ሜ አሸናፊ

– በዶሃው የአለም ሻምፒዮና በ10000ሜ 5ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

– ከአንድ ወር በፊት በህንድ የተካሄደውን የዴልሂ ግማሽ ማራቶን ውድደር በተከታታይ ለሁለተኛ አመት አሸንፏል፡፡

በሪሁ አረጋዊ – ሱር ኮንስትራክሽን

– ሰኔ 2010 በ ፊንላንድ ታምፔሬ በ ተካሄደው የአለም ከ20አመት በታች ሻምፒዮና በ10000ሜ ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ፡፡

– ሀምሌ 2010 በአልጄሪያ በተካሄደ የአፍሪካ ታዳጊዎች ሻምፒዮና በ3000ሜ አሸናፊ፡፡

– በጥቅምት 2011 ዓ.ም በአርጄንቲና በተካሄደ የአለም የታዳጊዎች ኦሊምፒክ በ3000ሜ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ፡፡

አቤ ጋሻሁን፡ ጆሴፍ ባባኒያዝ ስፖርት/አማራ ማረሚያ

– የ2009ዓ.ም – የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር አሸናፊ

– የ2011ዓ.ም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000ሜ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ

– በሞሮኮው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ5000ሜ አራተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡

ሀይለማርያም አማረ – ፌዴራል ፖሊስ

– ከአንድ ወር በፊት በፖርቱጋል ሊዝበን በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር 4ኛ ሆኖ ያጠናቀቀ፡፡

– በ2007ቱ የኮንጎ ብራዛቪል የአፍሪካ ጨዋታዎቸ በ3000ሜ መሰናክል የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረ

– በተመሳሳይ አመት አዲስ አበባ ላይ በተከናወነው የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና በተመሳሳይ የ3000ሜ ውድድር የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ

ሞገስ ጥዑማይ – መሶቦ ሲሚንቶ

– በ2009ዓ.ም የኢትጵያ ሻምፒዮና በ10000ሜ የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት

– በ2010ሩ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድደር ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ

– በ2006ዓ.ም የኢትዮጵያ ሻምፒዮና በ5000ሜ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *