ፎቶ:  ጋዜጠኛ ግርማ በቀለ፣ ካሳሁን ቃሲም እና አቶ ጋሻው – የሽልማት ኮሚቴው አመራሮች

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በየዓመቱ የሚያካሂደውን የምርጥ ስፖርተኞች የሽልማት ስነስርዓት ጥቅምት 29/2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ለሶስተኛ ጊዜ እንደሚያካሂድ ተቋሙ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል።

በዕለቱም በሁሉም የውድድር ዘርፎች በእጩነት ከቀረቡት 10 ተፎካካሪዎች መካከል ለመጨረሻው ዙር ፉክክር ያለፉ ሶስት እጩዎች ተለይተው ታውቀዋል። በዚህም መሰረት፦

ምርጥ አትሌት ዘርፍ ዕጩዎች

በወንዶች                                በሴቶች

– ሞስነት ገረመው                – ለተሰንበት ግደይ
– ሰለሞን ባረጋ                    –  ፋንቱ ወርቁ
– ጌትነት ዋለ                       – መቅደስ አበበ

በምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ዘርፍ ዕጩዎች

በሴቶች                                   በወንዶች

– ሴናፍ ዋቁማ                     – አማኑኤል ገብረሚካኤል
– እመቤት አዲሱ                  – ሱራፌል   ዳኛቸው
– ሰናይት ቦጋለ                     – ያሬድ ባየህ

የውድድሩ አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው የዋንጫ እና የ75,000 ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን፡ የህይወት ዘመን ተሸላሚ እና ለስፖርታዊ ጨዋነት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላትም ዕውቅና እንደሚሰጥም ተገልጿል።

የውድድሩ የከዚህ ቀደም አሸናፊዎች

የ2009 ዓ.ም አሸናፊዎች

በምርጥ አትሌት ዘርፍ            በምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች

በወንዶች – ሙክታር ዕድሪስ        በወንዶች – አስቻለው ታመነ
በሴቶች – አልማዝ አያና              በሴቶች – ሎዛ አበራ

የ2010 ዓ.ም አሸናፊዎች

በምርጥ አትሌት                    በምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች

በወንዶች – ሰለሞን ባረጋ       በወንዶች – አብዱልከሪም መሀመድ
በሴቶች – ገንዘቤ ዲባባ        በሴቶች – ሰናይት ቦጋለ

የህይዎት ዘመን ተሸላሚ – አሰልጣኝ ስንታየሁ እሸቱ

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *