ዶሃ – ኳታር – መስከረም 23/2012 ዓ.ም –  የ18 አመቱ ወጣት አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000ሜ መሠናክል ሁለተኛ በመውጣት የውድድሩን ሁለተኛ የብር ሜዳሊያ ለሀገሩ አሸንፏል፡፡  ለሜቻ ይህ ድሉ በአለም ሻፒዮናው ታሪክ በርቀቱ ለሀገሩ ሜዳሊያ ያሸነፈ የመጀመሪያው ወንድ አትሌት ያደርገዋል፡፡ አትሌት ሶፊያ አሰፋ ሞስኮ ላይ በ2013 ያገኘችው የነሀስ ሜዳሊያ እስካሁን ድረስ ለኢትዮጵያ በርቀቱ በሁለቱም ጾታ የተመዘገበ ብቸኛ ድል ነበር፡፡

በአለም አቀፍ ውድድር፡ ገና ለሶስተኛ ጊዜ የተሳተፈው አትሌት ለሜቻ፡ ከውድደሩ የከዚህ ቀደም አሸናፊ ኬኒያዊው ኮንሰስለስ ኪፕሩቶ ጋር እልህ አስጨራሽ ፉክክር አድርጎ፡ በመጨረሻም በአንድ ማይክሮ ሴኮንድ ብቻ ተቀድሞ በ8፡01.35 የኢትዮጰያ ክብረወሰን በሆነ ሰዓት የብር ሜዳሊያውን ሊያሸንፍ ችሏል፡፡ በርቀቱ የማሸነፍ ሰፊ ግምት ተሰጥቶት የነበረው የ2019ኙ የዲያሞንድ ሊግ አሸናፊው ጌትነት ዋሌ 8፡05.21 የግሉን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ  ሞሮኳዊው ኤል ባካሊን ተከትሎ አራተኝ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል በጥሩ የቡድን ስራ በተካሄደው በዚህ ውድድር፡ የመጀመሪያዎቹን ዙሮች በመሪነት ሲያፈጥን የነበረው ጫላ በዮ፡  ለመጀመሪያ ጊዜ አጥልቆት በሮጠው ጫም ምቾት በማጣቱ ምክንያት ውድድሩ ሊገባደድ ሁለት ዙሮች ሲቀሩት ለማቋረጥ ተገዷል፡፡

የአትሌቶቹ አስተያየት

ለሜቻ ግርማ ‹‹በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ እቅዳችን የነበረው በጥሩ የቡድን ስራ እየተጋገዝን በመሮጥ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያሉትን ሁሉንም ሜደሊያዎች ማሸነፍ ነበር፡፡ የርቀቱ የሀገራችን የመጀመሪያው የሜዳሊያ ባለቤት በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል፡፡››

ጌትነት ዋሌ ‹‹እቅዳችን ሁሉንም ሜዳሊያዎች ማሸነፍ ቢሆንም የብርሜዳሊያ በማግኘታችን ደስ ብሎኛል፡፡ አመቱን ሙሉ በርካታ ውድድሮች በማድረጌ ትንሽ አቅም አንሶኛል ግን የምችለውን ሁሉ ቸድርጌያለሁ፡፡››

ጫላ በዮ ‹‹እቅዳችን ከዚህ የተሸላ ውጤት ለማምጣት ነበር፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ አአድረጌው የገባሁት ጫማ በጣም ስላጣበቀኝ፤ መሮጥ እሰከሚያቅተኝ ድረስ አስቸግሮኝ ውድድሩን ለማቋረጥ ተገድጃለሁ፡፡››

በእለቱ ኢትዮጵያውያን በተሳተፉበት የ1500ሜ ወንዶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ታደሰ ለሚ 12ኛ በመውጣቱ እንዲሁም አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ውድድሩን በማቋረጡ ወደ ፍጻሜው ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡

ኳታራውያን፡ የሀገሪቱን ኢሚር ሞሀመድ አል ታኸኒን ጨምሮ፡ ብርቅዬው አትሌታቸው ሙታዝ ኢሳ ባርሺም የአለም የከፍታ ዝላይ የሻምፒዮናነት ክብሩን 2.37 በመዝለል በድጋሜ እንዲጎናጸፍ፡ ድጋፍ ለመስጠት ከየትኛውም ጊዜ በላይ የካሊፋ ስቴዲየምን ሞልተው በተገኙበት የሻምፒናው የእለት ስምንት ውሎ፣ የተለመደው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ዛሬም እንዳለፉት ቀናት ሁሉ፡ ለአትሌቶቹ ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ነበር፡፡

 የዕለት ዘጠኝ (መስከረም 24) የኢትዮጵያውያን አትሌቶች መርሃግብሮች

1500ሜ ሴቶች ፍጻሜ –  ተሳታፊ አትሌት – ጉዳፍ ጸጋዬ – ሰዓት – ምሽት 2፡55

5000ሜ ሴቶች ፍጻሜ – ተሳታፊ አትሌቶች – ሀዊ ፈይሳ፣ ጸሀይ ገመቹ እና ፋንቱ ወርቁ- ሰዓት – ምሽት 3፡25

ማራቶን ወንዶች –  ተሳታፊ አትሌቶች – ሞስነት ገረመው፣ ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሙሌ ዋሲሁን – ሰዓት – ሌሊት 5፡59

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *