መስከረም 17/2012 ዓ.ም – በዶሃ ኳታር ትናንት በተጀመረው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በተደረጉ የማጣሪያ ውድድሮች የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ሲሆን በሴቶች ማራቶን የተሳተፉት ሶስቱም አትሌቶች በውድድሩ አጋማሽ አቋርጠው ወጥተዋል፡፡

በነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ከከፍተኛ ውዝግብ በኋላ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ውድድር ከተሳተፉ 68 አትሌቶች 28ቱ ውድድሩን ለማቋረጥ የተገደዱ ሲሆን፤ ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው ኬኒያዊቷ ሩት ቼፔንጌቲች የገባችበት 2፡32፡43 ሰዓት የውድድሩ የምንጊዜም ቀርፋፋው ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በተጨማሪም ሩት ያሸነፈችበት ሰዓት ከወራት አስቀድሞ የዱባይ ማራቶንን ስታሸነፍ ካሰመዘገበችው 2፡17፡08 በ15 ደቂቃዎች ያክል የዘገዬ ሆኗል፡፡ እርሷን ተከትለው የገቡት ባህሬናዊቷ ሮዝ ቼሊሞ እና ናሚቢያዊቷ ሄላሊያ ጆሃነሰን የብር እና ነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊዎች ሆነዋል።

 

በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን የማጣሪያ ውድድር ላይ የተሳተፈቸው የ800ሜ ተወዳዳሪዋ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ከነበረችበት ምድብ አራት አምስተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ባስመዘገበችው 02፡02.71 ፈጣን ሰኣት ዛሬ ወደሚከናወነው የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ለማለፍ ችላለች፡፡

በ3000ሜ መሰናክል የሴቶች ማጣሪያ ከተሳተፉት መቅደስ አበበ ፣ሎሚ ሙለታ እና ዘርፌ ወንድማገኝ ከምድብ አንድ 9፡27.61 በሆነ የተሻለ ሰዓት አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችው መቅደስ አበበ ወደ ፍጻሜው ስታልፍ ከየምድባቸው 7ኛ እና 9ኛ ሆነው ያጠናቀቁት ዘርፌ ወንድማገኝ እና ሎሚ ሙለታ ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡

በእለቱ በነበረው የስታዲየም ውስጥ የመጨረሻ የኢትዮጵያውያን የማጣሪያ ውድድር: ከመጀመሪያው ምድብ አንደኛ እና ሶስተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ሰለሞን ባረጋ እና ሙክታር እድሪስ እንዲሁም ከምድብ ሁለት ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ጥላሁን ሀይሌ ወደ ፍጻሜው ሲያልፉ በዚሁ ምድብ 14ኛ ሆኖ የጨረሰው አባዲ ሀዲስ ወደ ፍጻሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡

ዕለት ሁለት

800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍጻሜ፡ ተሳታፊ አትሌት- ድርቤ ወልተጂ ፡ የወድድር ሰዓት ምሽት 1፡15

10000ሜ ሴቶች ፍጻሜ ፡ ተሳታፊ አትሌቶች – ለተሰንበት ግደይ፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ነጻነት ጉደታ፣ የውድድር ሰዓት – ምሽት 3፡10

የርቀቱ የከዚህ ቀደም አሸናፊዋ አልማዝ አያና በጉዳት ምክንያት በማትሳተፍበት በዚህ ውድድር፡ የርቀቱን የኢትዮጵያውያን የበላይነት ለማስቀጠል በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሻምፒዮናውን የመጀመሪያ ሜዳሊያ ለሀገራቸው ለማስመዝገብ በምሽቱ ፉክክር ላይ ይወዳደራሉ፡፡

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *