አዲስ አበባ – ነሐሴ 08/2011 ዓ.ም – የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ እግር ኳስ: የሊግ ውድድር ላይ የሚታየውን የአደረጃጀት: የአሰራር ስርዓት እና የሰው ሀይል ችግሮችን ለመለየት እና የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማስቀመጥ አስጠናሁት ባለው ጥናት ዙሪያ ከልዩልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጁፒተር ሆቴል ውይይት አካሂዷል።

በጥናቱ መሠረትም አሁን ያለው የውድድር አካሄድ: ከፋይናንስ አጠቃቀም: ከመዋቅራዊ አስተዳደር: ከእግር ኳስ መርህ: ከክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተሳትፎ: ከጸጥታ እና ከስፖርታዊ ጨዋነት: ከእግር ኳስ ልማት: ከስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋት: ከብሔራዊ ቡድኖቻችን እና ክለቦቻችን አለምአቀፋዊ ውጤታማነት አንጻር ባሉ መለኪያዎች ሲለካ ሙሉ በሙሉ አዋጪ አለመሆኑ ስለተረጋገጠ አዲስ አደረጃጀት እንደሚያስፈልግ አመላክቷል።እንደ ፌዴሬሽኑ እምነትም በዚህ ጥናት መሰረት ሁለት ዋናዋና ምክረ ሀሳቦች ተገኝተዋል።

  1. አሁን ያለው የሊግ ውድድር እና አሰራር በተቀመጡት መመዘኛዎች አዋጭ ባለመሆኑ አማራጭ የሊግ አደረጃጀትና አሰራር እንዲቀረጽ ማድረግ።
  2. ክልሎች ጠንካራ የውስጥ ውድድሮችን እንዲያደራጁ በማድረግ ጠንካራ እግርኳሳዊ ፉክክር የሚታይበት የሊግ ውድድር እንዲያካሂዱ ማድረግ እና የየክልሎቹ አሸናፊዎችን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በሚያካሂደው የማጠቃለያ ውድድር የኢትዮጵያ ሻምፒዮንን መለየት የሚቻልበት አደረጃጀትን መፍጠር የሚሉት መሆናቸውን ጥናቱን ያቀረቡት አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ገልጸዋል።

በጥናቱ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ 22ቱም ክለቦች ለተግባራዊነቱ ተሰማምተው ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን ቀጣዩ ሂደትም ሰነዱን ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ማቅረብ እንደሆነ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ሃይለእየሱስ ፍስሃ ገልጸዋል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *